ጉባኤ ኒቅያ
በቤተክርስትያን ታሪክ ከተነሱ መናፍቃን ሁሉ እንደ አርዮስ የከፋ የለም::
ኅዳር 9-እጅግ የከበሩ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ቅዱሳን አበው ሊቃውንት በ325 ዓ.ም በኒቅያ አርዮስን ያወገዙበት ዕለት ነው፡፡
አርዮስ መሠረታዊ ትምህርቱን በሊብያ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ እስክንድርያ በመጓዝ በእስክንድርያ ከፍተኛ ት/ቤት
ትምህርት አጠናቆ እንደጨረሰ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሄዶ በአንጾኪያ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት ገብቶ የትርጓሜ
መጻሕፍትና የነገረ መለኮት ትምህርት ተምሯል፡፡ በጊዜውም ሉቅያኖስ ከተባለ መናፍቅ ዘንድ ተምሯል፡፡ አርዮስ
አብዛኛውን የኑፋቄ ትምህርት ያገኘው ከሉቅያኖስና በአንጾኪያ ት/ቤት ከሚገኙ ሌሎች መናፍቃን ነው፡፡ በአንጾኪያ
ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ኑሮውን በዚያው አደረገ፡፡
እነዚህም እጅግ የከበሩ ቅዱሳን መጀመሪያ አርዮስን አስተምረው ለመመለስ መጀመሪያ በኒቅያ የተሰበሰቡት መስከረም 21 ቀን ነው፡፡ ከሃዲው አርዮስ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› ብሎ በመነሣቱ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዓመታት እንድትታወክና እንድትበጠበጥ ምክንያት ሆኗል፡፡
ከመስከረም 21 እስከ ሚያዝያ 21 ተጠቃለው ኒቅያ ገቡ:: በ325 ዓ/ም ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::
በጉባዔው ላይ ከተገኙት አባቶች መካከል ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ : ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ እና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ ይገኙበታል::
በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት::
በጉባኤው መጨረሻም አበው ሊቃውንት 318ቱ በአንዲትም ቃል ሆነው ዛሬ ላይ የጸሎታችን መጀመሪያ የሆነውን ‹‹ጸሎተ ሃይማኖትን›› ደነገጉልን ሃይማኖትን አጸኑልን፡፡
የከበረች በረከታቸው ድል የማትነሣ ረድኤታቸው ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው ከእኛ ጋር ትሁን ሥሉስ ቅዱስን ያለማጉደል ያለ መጨመር እናምናለንና ክፉዎች ሰዎች ከመከሩት ምክር ከሰይጣን ጠላትነት ታድነን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
መልካም ሰንበት

No comments:
Post a Comment